1. ግዴታ አለብን የወንጌል አደራ
ዛሬ ልንመሰክር የማዳኑን ስራ
እንዳንዘናጋ ሆነን ቸልተኛ
ወንጌሉን እንስበክ የነፍሳት መዳኛ
የተመረጠው ጊዜው አሁን ነው
ማንቀላፋቱ ምንድን ነው
የመከሩ ስራ ብዙ ነው /2/
2. በልብህ ውስጥ ያለ የበራልህ እውነት
ዛሬም እድሉ አለህ ተው ተጠቀምበት
እንመስክር ለሌላ የምስራች ቃሉን
እውነት መንገድ ህይወት ኢየሱስ መሆኑን
የተመረጠው ጊዜው አሁን ነው
ማንቀላፋቱ ምንድን ነው
የመከሩ ስራ ብዙ ነው /2/
3. ታጥቀን እንነሳ ወንጌሉ ይስፋፋ
በጌታ ኢየሱስ በእምነት ሙሉ ተስፋ
የዲያቢሎስ መንገድ በቃሉ ይደምሰስ
ምርኮንም እናብዛ መንግስቱን የሚወርስ
የተመረጠው ጊዜው አሁን ነው
ማንቀላፋቱ ምንድን ነው
የመከሩ ስራ ብዙ ነው /2/
