አፍቅሮና ፈቅዶ ፈጥሮኝ
ለተሻለ ነገር አጭቶኝ
እኔ ግን በደልኩት መች ገባኝ
ይበልጥ ወደደኝ እራሱን ሰጠኝ
ከሰማይ ዙፋን መውረዱ
እራሱን ዝቅ ኣድርጐ መዋረዱ
ደሙን ያፈሰሰው ለእኔ
ለጥቅሜ ነው ሞቱ መድህኔ
እኔስ ብዬ ነበር ለምን /3/
ጌታዬ ሲጠራኝ እኔን /3/
በስሜ ና ሲለኝ ንመኝ
ምኔን አይቶ ጌታ ወደደኝ
ብትረሳ እንኳን ልጇን እናት
የእኔ ፍቅር ጥልቅ ነው በውነት
ሲል እንደማለልኝ አሳየኝ
የእኔን ሞት ወስዶ አዳነኝ
