ስሜን ሰማሁ

169

ስሜን ሰማሁ አምላኬ ሲጠራኝ
ጠማማውን ውስጤን ወስዶ ሊያቀናው
ስሜን ስማሁ አምላኬ ሲጠራኝ
ሀዘኔን ተመልክቶ ደስታን ሊያለብሰኝ
ስሜን ስማሁኝ ስሜን ስሜን ሰማሁኝ

የጠራኝን አውቃለው አልቀርም እሄዳለው

ያስጨነቀኝን በሙሉ ለርሱ እነግረዋለው
አገልግለኝ ብሎኛልና አገለግለዋለው
እርሱ እኔን እንደወደደኝ እኔም እወደዋለው

አምላኬ ፈልጎኛል ከህዝብ መኃል ጠርቶኛል
አገለግለዋለው አገልግለኝ ብሎኛል
በእርሱ መመረጥ ፀጋ ነው ከሃብት በላይ ሃብት ነው
እኔ የአምላኬ ነኝ እግዚአብሔርም የኔ ነው

ስሜን ሰምቼ አምላኬ ጋር ሄጄ
የሰማዩን ሃብቴን ርስቴን ወስጄ
ስሜን ስሰማ አምላኬ ጋር ሄድኩና
ምሬቴን ቀየረልኝ አፌን ሞላው ምስጋና
ስሜን ሰምቼ ስሜን አፌን ምስጋና ሞልቼ

ኑሮ ከእግዚአብሔር ጋር ኧረ እንዴት ይመቻል
ሁሉ ካለው ደግ አምላክ መጠጋጋት ይበጃል
ለችግሬ መፍትሄ ከእርሱ መች ይታጣል
ሁሉንም ነገር ትቶ የእርሱ መሆን ያዋጣል

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top