ከተጠሩት መሐል

172

ከተጠሩት መሐል እዳልሄድ ኮብልዬ
ከምርጦችህ አንዱ አድርገኝ ጌታዬ

አንተን ለመከተል ጉዞ የጀመሩ
ዳሩ ግን ሰመንገድ ዝለው የሚቀሩ
የፈተና ማእበል ድል የሚነሳቸው
አሉ ብዙ ሰዎች አንተ የምታውቃቸው

ቃልህን የሚሰሙ አንተ የጠራሃቸው
ክርስቲያን ወገኖች እጅግ ብዙ ናቸው
ነገር ግን ጌታ ሆይ አንት ተናግረሐል
የምርጦቼ ቁጥር ጥቂት ነው ብለሃል

አለምን ሰይጣንን ስጋን አሸንፈው
ሊጓዙ የሚችሉ ድልን ተቀናጅተው
የፅዮን አርበኞች ሐይል የሞላቸው
ጌታ ሆይ ምርጦችህ እጅግ ጥቂት ናቸው

ልብህ መቅደስን አናስደፍር ብለው
እስከመጨረሻው ተዋግተው ተጋድለው
ወደአንተ የመጡት ድልን ነስተው

እኔንም አስታጥቀኝ ፀንቼ እንድዋጋ
ሐይልህን ሙላብኝ ሁልጊዜ እንድተጋ
የላዩን ትቼ ልጓዝ ወደፊቴ
በጉዞዬ ምራኝ ሁነኝ እረዳቴ

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top