ማርያም መሪያችን

183

የኛ መሪ ኮከብ በአፀያፊው አለም
አዛኝ እናታችን ምሪን ለዘለአለም
በሐጥያታችን ምክንያት ብንርቅም ካንቺ
ማርያም ነሽ ብለናል የታሰረን ፍቺ

በፍርድ ቀን እላይ በልጅሽ መንግስት
አቅፈሽ ደግፊን አውጭን ከጥፋት
ክብር ይገባሻል ማርያም የኛ እናት /2/

ገና አላለቀም መራራው ኑሮአችን
ጭንቃችንን አይተሽ አውጭን መሪያችን
በእናትነትሽ ያመነበት ሁሉ
ተኮንነው አይቀሩም ነፍሳት ይድናሉ

የክርስቶስ እናት ቅድስት ማርያም
እጅግ ንፅህት ነሽ ከሴቶች ከሁሉም
ከእንግዲህ ሁላችን ወደአንቺ መጥተናል
ሰላምና ፍቅርን ከአንቺ ተጠምተናል

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top