ክብርና ምስጋና ማርያም ይድረስሽ
የዘውትር ተስፋችን አንቺ ስለሆንሽ
በሰማይ ክዋክብት በፍፁም ታጅበሽ
በመላእክት ፊት ከብረሽ ተመስግነሽ
በመንገስተ ሰማይ ታላቅ ክብር ያለሽ
ለኛ ለሁላችን እመቤታች ነሽ
መላእክት ወደሱሽ በአንቺ ስላለ ክብር
ስላቺ ምስጋና እኛም እንዘምር
ወድቀን ተንበርክከን ከመንበርሽ ስር
በአንቺ ይታደለን የሰማያት ክብር
ፍልሰታ ማርያም መላእክት የከበቡሽ
ሊቃውንት በህብረት ለአንቺ የዘመሩልሽ
የአዳም ሐጥያት ከቶ ያልዳሰሰሽ
በረቂቅ ውበትሽ ከእንቁ የነጠርሽ
በቅድስት ስላሴ ፍፁም የተባረክሽ
ቅዱሳን ስለ ክብርሽ በውነት ያወደሱሽ
ሁሉም ስለ ፍቅርሽ የሚዘምሩልሽ
ለአንቺ ነው እመቤት ምስጋና የሚገባሽ
ይህ አመት ለአንቺ ነው ደጓ እናታችን
ረሐብ ጦርነትን አንሺ ከአገራችን
ኢትዩጵያ እርስትሽ ናት የልጅሽ ሰጦታ
ሕዝቧን ጠብቂላት ሁኝላት መከታ
