እንዴት ብርቅ ነው የእናት ልብ
የጠራሽ ነሽ ኦ ማርያም
ሌላው ፍቅር ቢለዋወጥ
ያንቺ ፍቅር የዘለአለም
ባሕር በንዴት ሲቆጣ
ምን ይሆን መጥለቅ ሲመጣ
የጠራሽ ኮከብ ነሽ ስታበሪ
የሰማይ ሰላም የምታመጣ
አደራ ልቤን ተቀበይኝ
በዛሬው ቀን ላገልግልሽ
ፍቅሬ ለአንተ ነው በይኝ
ከልቤ በቅን ላሞግስሽ
ከክርስትናዬ ቀን አንስቶ
ከእኔ አልተለየሽም ከቶ
ልቤ በፍቅርሽ ተሞልቶ
ሊወጣ አይችልም ተሳስቶ
አንድ ቀን እሰማይ እርስታችን
አንችን ስንከብ ነው ደስታችን
ኦ ማርያም አንቺ ነሽ ተስፋችን
እዚያ የምትሆኚ ዘወትር ፍቅራችን
