ታምራዊ ማህፀን ፍሬው የከበረ
አዳኝ ፈዋሽ ጌታ ለአለም ያኖረ
ፀጋው የማይነጥፍ ፍፁም የማይጐልድል
እንደተባረከ ዘላለም ይኖራል
ብፅእት ማርያም አንቺ ቅድስት
ትውልድ ሁሉ ይላል ብጽዕት
ለአለም ሕይወት የሰጠሽው
ክብር ላንቺ ይድረስሽ
በችግርም ጊዜ መፍትሔ አፍላቂ
በጨለማችን ውስጥ ብርሃን ፈንጣቂ
የዘመናት ሃጢያት ከፊታችን ኣጥፊ
የማህፀንሽ ፍሬ ታምራቱ ሰፊ
የህልውናችን ትርጉምን ፈጣሪ
የዘላለም ሕይወት በረከት አብሳሪ
የፍዳውን ዘመን በምህረት ቀያሪ
ያማህፀን እኮ ነው የዚህ ሁሉ ሰሪ
