ምንስ ይባላል

223

ማንንም አስቀይመህ አታውቅም የማንም ባለዕዳ አይደለህም
ሁሉንም በፍቅር ታያለህ ፊት አይተህ መች ታያላለህ
ከፍቅርህ አንዳች አታጎድልም ጽድቅህን የሚከሰው የለም
በእውነት በቅን ትፈርዳለህ በሰማይ በምድር ጌታነህ

ምንስ ይባላል ምንስ ይመለሳል እረ ላንተ ጌታ /2/
ለቅድስናህ መጀመርያ የለው /2/
ላምላክነትህ መጀመርያ የለው /2/
ለፍፅምና መጀመርያ የለው /2/
ለዕድሜህ መነሻ መጨረሻ የለው /2/

አንተ ጌታ ነህ የለም የሚመስልህ
አንተ ጌታ ነህ ማነው የሚከስህ /2/
አንተ ጻድቅ ነህ የለም የሚምልህ

አንተ ጻድቅ ነህ ማነው የሚወቅስህ /2/

በሰማይ ዙፋንህ ተቀምጠሀል ምድርን በእግር ረግጠሀል
ዓይኖችህ ይመለከታሉ የተሰወረውን ያያሉ
ለሀጢያተኛው ለጻድቁ ፀሃይ ዝናብ ትሰጣላህ
አንደኛውን ከአንደኛው ሳትለይ ፅድቅህን ትፈፅማለህ

ምንስ ይባላል ምንስ ይመለሳል እረ ላንተ ጌታ /2/

ለሀብት በውብ አትማለክ አትባል በሀሰት ፈርድክ
ችሎትህ ሁሌ እውነት ነው ሚዛንህ ትክክለኛ ነው
ማንም እጁን አይዘረጋም በስራህ ጣልቃ አይገባም
ሁሌ ጊዜ መልካም ታደርጋለህ የሰላም የፍቅር ጌታ ነህ
ምንስ ይባላል ምንስ ይመለሳል እረ ላንተ ጌታ /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top