ከዘላለም በፊት /3/ ዘመን ቢገኝ እንኳን
ከዘላለም ኋላ /3/ ዘመን ቢገኝ እንኳን
አንተ ግን መጀመሪያ የለህ
አንተ ግን መጨረሻ የለህ
ጌታዬ መጀመሪያ የለህ
አምላኬ መጨረሻ የለህ
ለምድር መሠረት መጀመሪያ አለት
አንድ ሁለት ተብሎ የሚቆጠርለት
ለሁሉም መነሻና መድረሻ አለው /2/
ያንተ ግን ጌታዬ ከማንም ልዩ ነው
ከማንም ጋር አላወዳድርህም
ከማንም ጋር አላመዛዝንህም /2/
ጌታ ነህ /3/ ዘለአለም /4/
አዳምን ከአፈር በእጅህ ስታበጅ
ሊኖርባት ምድርን ፈቅደህ ስታዘጋጅ
ማን ነበር ያን ጊዜ ቆሞ ያማከረህ
በምድር እንዲያበዙ ሠውን የባረከ
ያኔ ነበረሱ የሚል ማንም የለም /4/
ብቻህን /2/ ጌታ ነህ ለዘለአለም
ብቻህን /2/ አምላክ ነህ ለዘላአለም
ቀንና ሌሊቱን እኩል ስትከፍል
ፀሀይ በስርዓትህ ጊዜ ስትሰለጥን
በጨረቃ ድምቀት እጅ የገባ ማንነው
የከዋክብቱ ውበት ሚስጥሩ የአንተው ነው
የኔ አገዝኩህ የሚል ማንም የለም
አማከርኩህ የሚል ማንም የለም
ጌታነህ ጌታ ነህ ጌታ ነህ ለዘላለም
ጌታነህ ጌታ ነህ ለዘለዓለም
