የምኖረው ባንተ ነው የኔ ጌታ አ ሀ ሀ
የምኖረው ባንተ ነው የኔ የሱስ ሁሁስ
እኔ ምንም ፅድቅ የለኝ የማወራ አ ሀ ሀ ው
በምህረትህ ብዛት ነው የምኖረው
ከቅዱሳን ጋራ ገድልን ከሰሩ
ራሴን ሳወዳድር አንተን ካስከበሩ
የመርገም ጨርቅ ነው አምናለሁኝ ፅድቄ
በምህረትህ ብዛት ኖራለሁ ደምቅ
እንደ እኔማ ሲሆን እንደ ክፉነቴ
በተረሳሁ ነበር ጠፍቶ ማንነቴ
ግን እየበዛልኝ ያንተ ቸርነት
ይኽው እኖራለሁ አለሁኝ በሕይወት
ሲነጋ እነቃለሁ አልፎልኝ ሌሊቱ
ሲመሽም አርፋለሁ ደግሞ በምሽቱ
ግን ብርታት የለኝም እኔ ህን ልሰራ
አምላኬ አንተ ነህ ለዚህ ምትጠራ
