አንተ ግን ትልቅ ነህ

242

በላይ በዙፋንህ በክብር ያለኸው
ምድር የእግሮችህ መርገጫ የሆነው
እልፍ አዕላፍ መላዕክቶች የሚዘምሩልህ
ቅዱስ እግዚአብሔር አንተ ግን ትልቅ ነህ

ሚያምር ዜማ ስግደትን ጨምሬ ቅዱስ
መላዕክቶች ጋር በአንድነት አብሬ ቅዱስ
ቀንና ሌሊቱን አንተን አመልካለው ቅዱስ
ጋድቄ በፊትህ ላንተ እሰግዳለው ቅዱስ

ቅዱስ እግዚአብሔር የሁሉ የበላይ ቅዱስ
እንዳንተ አላየሁም በእርግጥ ኤልሻዳይ ቅዱስ
አክብሮቴ ሁሉ ማደሪያህን ይሙላው ቅዱስ

በመልካም መዓዛ መቅደስህን ይጠነው ቅዱስ

የልቤን አውጥቼ ብዘምርልህ ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ እያልኩ ሁሌም ባመልክህ ቅዱስ
እግዚአብሔር አምላኬ ላንተ ያንስብሃል ቅዱስ
ላንተ ሚመጥንህ ምን ይገኝልሃል ቅዱስ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top