ከአብ ዘንድ ተልክህ ልታድነን
የመከራ ፅዋ ጠጣህልን
በአንተ ቁስል እኛ ተፈወስን
በመከራህ ምህረት አገኘን /2/
ያለ በደልህ ሲፈርዱብህ
ባልገባቸው ነገር አንተን ሲወነጅሉህ
እንደሚሸለት በግ ስትነዳዕ
የእኛ ባንተ ሲሆን የሞት ዕዳ
የእሾህ አክሊልን ሲደፉብህ
አንገላተው አንተን መከራን ሲያበዙብህ
ክብር ላንተ ይሁን የአይሁድ ንጉሥ
ብለው ሲያፌዙብህ ምንም አላልክ
በመስቀል ላይ ሆነህ ተቸንክረህ
ይቅር በላቸው አልክ አላወቁም ብለህ
ሲሳለቁብህ ሲሰድቡህ
ለኛ ነበር ለካ መከራህ
