ስራህ ብዙ ነው

247

የኔስ አምላክ/የኔ ጌታ ስራህ ብዙ ብዙ ብዙ ነው

ባወራውም ብተርከው አያልቅ ብዙ ነው /2/

ፀጋህ አልጎደለኝም ለኔ ለልጅህ
መቼም አትሰስትብኝ ጌታ ምህረትህን
አምላኬ ሳወድስህ እጅግ ደስ ይለኛል
በዝማሬ ሳመልክህ ልቤን ያረካኛል

የኔ ጌታ ላወድስህ ላክብርህ
ረዳቴ ሆነኸኛል ላወድስህ

እንዴትስ እችላለው በቃላት ዘርዝሬ
ተነስቼ ላክብረውይኸው በዝማሬ
የምድሩን ትቶ ሰው ወደአንተ ቢጠጋ
ደርቦ ይኖር ነበር በፀጋ ላይ ፀጋ

የኔ ጌታ ላወድስህ ላክብርህ
ረዳቴ ሆነኸኛል ላወድስህ

ተስፋ አጥቼ ስኖር ያኔ በጨለማ
ቃልህ ቢርበኝም ፍቅርህን ብጠማ
አንተ ግን ደጉ አምላክ ምህረትህን ገለጥከው
ልጅህን ለህይወቴ በፍቅር ሰዋኸው
የኔስ አምላክ….

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top