የጠራህ ያፈቀርከኝ

257

የጠራህ ያፈቀርከኝ ኢየሱስ ጌታዬ
የዘላለም ምርጫዬ ነህ የመጨረሻዬ
ቢወራ ቢገለጽ የሰጠኸኝ ደስታ
ተወደስ ልበልህ የነፍሴ አልኝታ
ምንን እከፍላለሁ ለዋልከው ውለታ
ተመስገን ልበልህ ጠዋት ሆነ ማታ /4/

ስምህን ጠርቼ ብነግርህ መሆኔን ከርታታ
በፍቅር አይተኸኝ ለወጥክ ሁካታዬን በደስታ
እንደ ፍቅርህ ብዛት ሰው ሆኜ በቤትህ ቆሜያለሁ
ለዘላለም ጌታ ካንተ ጋር እኖራለሁ
የጠራህ ያፈቀርከኝ……

ለውለታህ ምላሽ ቢሆን ልገዛልህ ኢየሱሴ

በሄድኩበት ሁሉ ታክብርህ ታንግስህ ምላሴ
ለዚህ ያበቃኸኝ አንተ ብቻ እኮ ነህ አምላኬ
ላመስግንህ ዛሬም ፊትህ ተንበርኬ
ቢወራ ቢገለጽ …..

ፍቅርህ ማያቋርጥ መሆኑን ዘወትር አውቃለሁ
በህይወቴ ሁሉ ምስጋናን ለአንተ እቀኛለሁ
በፍቅርህም ምራኝ የኔ ታላቅ አምላክ ጌታ
ፍጹም ይረዳኛል እኔ እንዳልረታ
ምርጫዬ ነህ ምርጫዬ /2/
የግሌ ነህ የግሌ /2/
በልቤ ውስጥ የሾምኩህ
ጌታዬ ነህ ጌታዬ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top