ኧረ እንዴት

272

1. አስቤ እሮጬ ማልዘልቀው
እቅዴን ኢየሱስ አሳመረው
ባምላኬ ጣፍጦልኝ ኑሮዬ
ለምልሞ አየሁት ተስፋዬ /2/

ኧረ እንዴት /2/ ልርሳዉ
ውለታው ውስጤን ከበደዉ
አልቻልኩም እንደው ዝም ማለት
ተነሳሁ ልመሰክርለት

2. ያለፍኩት ያን ሁሉ በህይወቴ
በእርሱ ነው ኢየሱስ እረዳቴ
ዛሬ እንዴት አስችሎኝ ልለፈው
ውለታው ኧረ እንደምን ልርሳው /2/

ኧረ እንዴት /2/ ልርሳዉ
ውለታው ውስጤን ከበደዉ
አልቻልኩም እንደው ዝም ማለት
ተነሳሁ ልመሰክርለት

3. ጠላቴ ሲመኝልኝ ሞቴን
ጌታ ነው የተቤዣት ነፍሴን
እንደ ህልም ሁሉም አለፈና
ለወጠው ታሪኬን እንደገና /2/

ህይወቴ ያማረው በእርሱ ነው /2/
ነገሬ ያማረው በእርሱ ነው /2/

ጌታን ተደግፌ ያለፍኩትን ዘመን
ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው
በእኔ አቅም ብርታት
ይታለፋል ማለት ዘበት ነው
ጌታ ሆኖልኝ አቅም ብርታቴ
ዛሬን አየሁት አምሮ ሀይወቴ

ኧረ እንዴት /2/ ልርሳዉ
ውለታው ውስጤን ከበደዉ
አልቻልኩም እንደው ዝም ማለት
ተነሳሁ ልመሰክርለት

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top