ምን አይነት ፍቅር ነው
ኧረ ምን አይነት ፍቅር ነው
ስለ እኔ በመስቀል ላይ የዋለው
ኧረ እርሱ እንዴት ድንቅ አምላክ ነው /2/
ፍቅሩ ለየት ይላል ከሰው ልጅ ፍቅር
ስለ እኔ ብሎ ደሙን ያፈሰሰው ሚስጥር
እኮ ማነው ለፍቅር እንዲህ የሚሰቃይ
ጌታዬ ብቻ ነው ተሰቃይቶልን የሞተው
ኢየሱስ ብቻ ነው ተሰቃይቶልን የሞተው
ዕርቃኑን ተሰቅሎ መራራውን የጠጣው
ስለሀጥያቴ ብሎ ራሱን ያዋረደው
በመስቀል ተሰቅሎ ምህረት የማለደው
ኧረ እርሱ እንዴት ድንቅ አምላክ ነው /4/
ሞተሀል /2/ ስለኔ ………..አዎ ስለኔ
የሾህ አክሊል ደፍተህ ስለኔ ………..አዎ ስለኔ
በረሃብ በጥማት ተገርፈህ ………..አዎ ስለኔ
በእንጨት መስቀል ላይ ለኔ ………..አዎ ስለኔ
እንደሚታረድ በግ ዝም ብለህ ………..አዎ ስለኔ
እርግማኔን አበሳዬን ወስደህ ………..አዎ ስለኔ
እንዲህ የወደድከኝ /3/
ጌታ ሆይ እኔ ማነኝ
እንዲህ ያፈቀርከኝ /3/
ጌታ ሆይ እኔ ማነኝ
