ኧረ እንዴት እረሳለው

273

ኧረ እንዴት እረሳለው/4/
የረዳኸኝን የከፈልክልኝን
ኧኔ እንዴት ረሳለሁ ባንተ የሆንልኝን

ተንከባክበኸኝ እንደ እናት እንዳባት
አሳድገኸኛል ሆነኸኛል ሞገስ /2/
ክብሬም አንተው ነህ ማእረጌ ጌታ
ሁሉን ያለፍኩብህ ያንተን እንዴት ልርሳ /2/

ቃላቴ አይገልጸውም አቤት ያንተን ስራ
ካይምሮዬ ሰላይ ነው ባወራው ባወራ
እኔ ምስክር ነኝ በህይወት ዘመኔ
ከቶም አልረሳውም ውለታህን እኔ

ክብሬ /2/ እግዚአብሔር ነህ ሞገሴ

የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ ጌታ
የእኔ ወግ ማእረጌ አንተ ነህ ጌታ
የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ ጌታ
የበረከቴ ምንጭ አንተ ነህ ጌታ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top