- ገጸ በረከቴ ክብሬ ለእኔ ሀይሌ
በልጅሽ ተፍቋል ያ ክፉ በደሌ
እኔም አምንሻለሁ አማላጅ ነሽ ለእኔ
ወጣሁ ተማጽኜሽ ከዛ ከኩነኔእናትነትሽን መች አዘነጋለሁ
የመዳን በሬ ነሽ እኔም አምንሻለሁ
አማልጅኝ እያልኩኝ ደጅሽ እጸናለሁ
ከልካይ በሌለበት ማርያም /2/ እልሻለሁ - ሽልማቴ የእኔ እናት መአዛዬ
መውጫዬ መሰላል ሆንሽልኝ አርማዬ
ጽኑ እምነቴ ነሽ ንጽህት ኪዳኔ
አሻግሬ ያየሁሽ ታማኝ ነሽ የኔ - ጠጥቼ የረካሁብሽ የጥም ውሀዬ
ማርያም አንቺው ነሽ ለእኔ መመኪያዬ
ጨለማውን ረቺ ኢየሱስን የወለድሽ
ትውልድ ሁሉ ብጽእት ንጽህት የሚሉሽ
