የቱ ምሁር

276

የቱ ምሁር /3/
ይገልጸዋል ያንተን ክብር /2/

ትላንት ከገባኸን በላይ ሆነህ ታላቅ

ዛሬም ከምትገባን በላይ ሆነህ ታላቅ
ቃላት እንዴት ይገልጽሀል አንተን ከቶ
ክብርህ ሰማይና ምድርን እንዲሁ ሞልቶ

ይሁን በገባኸን መጠን ብቻ /2/
ያለንም ይሄ ነው ይሄ ብቻ /2/
ክብርህን እንወድስ ስምህን እንቀደስ
ከፍ በል የእኛ ሞገስ
እግዚአብሔር ክብር ይድረስ

ፍጹም በሚወደድ በቃላት መረጣ
መንፈሳዊ ቅኔ ካንደበት ቢወጣ
ክብርህን ባይገልጽም ማን ይተዋል ደክሞ
ይጨምራል እንጂ ደጋግሞ /2/
ትላንት …

ልክህን ያወቀ በምርምር ደርሶ
ማነው የጎበዘ ክብርህን ገልጾ ኣልፎ
ምንጭ ያገኛል እንጂ በጉዞው እንደገና
ሁሌም የሚዘመር የበዛ ምስጋና
ይሁን …

ባመራርህ ጻድቅ ፍርድህ የነጠረ
ሰማይና ምድር በጭብጥህ የኖረ
ዘላለማዊ ነህ ዘመንህ አይለካ
ትውልድን በትውልድ ብትቀይር ብትተካ
ትላንት…..
ይሁን…..

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top