ደመራ

278

መስቀል አብረሃ በከዋክብት

አሰርገወ ሰማይ እምኩሉሰ ፀሀየ አርአየ /2/

የፅናት ምልክት ችቦን እያበራን
እንዘምራለን ደመራውን ከበን
የብርሃን ጌታን ለሁሉ እንነግራለን
ለሞት ለትንሳኤው ምስክሮች ሆነን

አሜን ምስጋና ይብዛለት
ላዳነን እንዘምርለት
እሰይ ምስጋና ይብዛለት
ላዳነን ክብር ይሁንለት

አፅናኝ አባታችን ይመስገን ሁሌም ይመስገን
ደጋፊ አምላካችን ይመስገን ዛሬም ይመስገን

ቃልኪዳን ይታደስ ዛሬ በዚች እለት
መስቀል ተሸክመን በስሙ እንፅናለት
ፍሙን ስንሻገር በደስታ ተሞልተን
የቀራንዮን ታሪክ ደግመን እየሰበክን

የጠፋውን መስቀል መገኘት ስናስብ
የመስቀል መስዋዕትን እናስታውሳለን
የደሙ ፍሬዎች በጣሩ የወለደን
አርነት ወጠናል በደሙ ተዋጅተን

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top