እምዬ አንቺን እንወድሻለን

285

ቀድሞ የነበር ቃል በትንቢት የተባለው
በእስራኤል አምላክ ቃልም የተገባው
ከልጅ ልጅ ተወልጄ ድግሞም የማድነው
እማማ አንቺ ነሽ ለዚያ መልስ የሆንሽው /2/

እምዬ አንቺን እንወድሻለን
ማርያም አንቺን እናከብረኛለን
የጭንቅ አማላጂ እናፈቅርሻለን
የዘላለም አምላክ ባንቺ ስላገኘን

ለውዴ ማደሪያ ሲፈለግ በአለም
በዚም በዚያም ሲባል ፈጣሪ አላገኘም
ዝቅተኛይቱን አንቺኑ አገኘና
መቅደሱ አደረገሽ በፀጋው ሞላና /2/

በእምነት እኮ ነው ሁሉን የተቀበልሽ
የድሆችም እናት ተብላሽ የተጠራሽ
የጨካኙን እራስ በእግርሽ ስር ያረግሽው
እናቴ አንቺ ነሽ ደምቀሽ የታየሽው /2/

በቃና ሰርግ ላይ ያንች ስራ አለበት
ከልጅሽ ተማክረሽ ያዳንሽን ከውርደት
ታላቅ ስፍራ አለሽ ከልባችን ማህደር
አማላጅነትሽ ዘውትር ማይሰወር /2/

የሰላም ደብር ነሽ የፅሞና ማማ
የፍቅር እናት ነሽ አንራቅሽ እማማ
ፀጋን የሞላሽ ሆይ የፈጣሪ እናት
እንለምንሻለን እንድናገኝ ምህረት /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top