ነፍሴ በእግዚአብሔር ሀሴት ታደርጋለች
መንፈሴም በአምላኬ ሁሌ ትደሰታለች
እኔን ዝቅተኛ ባሪያውን ተመልክቷል
ትውልድ ሁሉ ቅድስት ብፅዕት ይለኛል /2/
- ዝቅ ያለውን ሊያነሳ ትዕቢተኛን ለጥል
ጌታ ኢየሱስ መጥቷል ምስኪንን ሊያከብር
እግዚአብሔር ሞገሴ ክብሬ ሆኖልኛል
የከበረው ንጉሥ በእኔ ሊያድር ወዷል
ነፍሴ በእግዚአብሔር ሀሴት ታደርጋለች
መንፈሴም በአምላኬ ሁሌ ትደሰታለች
እኔን ዝቅተኛ ባሪያውን ተመልክቷል
ትውልድ ሁሉ ቅድስት ብፅዕት ይለኛል /2/
2. ከብዙዎች መሐል ታማኝ አድርጎ ቆጥሮኝ
የማዳኑን ምስጢር ተካፋይ አረገኝ
ነፍሴም ተማረከች በሆነላት ነገር
ጌታ የዋለላትን ትመስክር ዘወትር
ነፍሴ በእግዚአብሔር ሀሴት ታደርጋለች
መንፈሴም በአምላኬ ሁሌ ትደሰታለች
እኔን ዝቅተኛ ባሪያውን ተመልክቷል
ትውልድ ሁሉ ቅድስት ብፅዕት ይለኛል /2/
3. ብርቱ የሆነው ጌታ ድንቅ አድርጎልኛል
የቅዱስ መንፈሱ እግዚአብሔር ዳሶኛል
የመለኮት ኃይሉን ጥበቡን አሳየኝ
ማዳኑን ለማየት በኩር አደረገኝ
ነፍሴ በእግዚአብሔር ሀሴት ታደርጋለች
መንፈሴም በአምላኬ ሁሌ ትደሰታለች
እኔን ዝቅተኛ ባሪያውን ተመልክቷል
ትውልድ ሁሉ ቅድስት ብፅዕት ይለኛል /2/
