ለእኔ የለም ካንተ በላይ
በሕይወቴ ገኖ የሚታይ
ክንደ ብርቱ ለዘለዓለም
እንደ እግዚአብሔር ያለ የለም
1. የፍጥረታት ንጉስ የጌቶች ጌታ /2/
ካንተ ጋር ሞግቶ ማነው የሚረታ /2/
ለሚታመኑብህ ታስተማምናለህ /2/
ቢወራረዱብህ መች ታሳፍራላህ /2/
ምስክርነት እሠጣለሁ
እኔም አንዱነኝ ክብሩን ያየሁ
ከፊት ለፊቴ እየመራኽኝ
ያማረ ሕይወት አሳየኽኝ
2. የባዖል ነቢያት የታመኑበት /2/
ምክንያቱ ምንድ ነው የዘገየበት /2/
ባንድ ጥሪ ብቻ ሰምቶ ሚመልሰው /3/
የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ ነው
አሃ እኔ የማመልከው /2/
ህያው አምላክ ነው ይመልሳል
ታምኖ ለጠራው መች ዝም ይላል
ዛሬም በእርሱ ክንድ ለታመኑ
በሰማይ አለ በዙፋኑ /6/
