1. ካንተ የተነሳ በሆነልኝ ነገር
ከማመስገን በቀር እኔ ምን ልናገር
አስበህ አቅደህ ለሰጠኸኝ በሙሉ
ጌታ ስምህ ይክበር አመሰግንሃለሁ
ከኔ የሆነ የለም አንድም አልለፋሁም
እንዲያው ሰጥተኸኛል ይህን አልረሳሁኝም
ስለዚህ ጌታዬ ለእኔ ስላሰብከው
አድርገኽልኛል ከአእምሮዬ በላይ
ጌታዬ ተባረክ በምድርም በሰማይ /3/
አዝ. አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ /3/
2. እድሜዬን በሙሉ ብለፋና ብጥር
የማላገኘውን ሰማያዊ ሚስጥር
ለልቤ ተናግረህ ልቤንም ባረከው
ከዚህ ሁሉ በላይ የራስህ አደረግከው
እኔም ተስማምቼ በፍቅርህ ተማረኩ
ጌታዬ አምላኬ ምርጫዬ አደረግኩህ
አንተ ከመረጥከኝ ወዴት እሄዳለሁ
ካንተ የበለጠ ምንስ አገኛለሁ
ጌታዬ አምላኬ በህይወቴ ላክብርህ
ይሄ ነው ምኞቴ ዘመኔን ልሰጥህ
ይሄ ነው መሻቴ እድሜዬን ልሰጥህ /3/
አዝ. አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ /3/
