ደስታን አብሳሪ
ደስታን አብሳሪ ምስራች ነጋሪ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ናልን ከሰማይ
1.ለማርያም በናዝሬት እንዳበሰርካት
ተቀብለህ ስጠን የሰላም መልዕክት
በጦርነት በረሀብ ተቃጥለናልና
የምስራቹን ቃል ቶሎ ይዘህልን ና
ደስታን አብሳሪ ምስራች ነጋሪ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ናልን ከሰማይ
2.በጣሞ ስንደክም ከኋላ ስንቀር
አማልደን ከጌታ ወድቀን እንዳንቀር
ቃልህ የሚጣፍጥ ሳለ እንደማር
አሁንም አሁንም ደጋግመህ አብስር
ደስታን አብሳሪ ምስራች ነጋሪ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ናልን ከሰማይ
3.የደስታን ዜና ይዘህ የምትመጣ
በዓለማችን ላይ ሰላም እንዲመጣ
የምስራች ንገር ለአሕዛብ በሙሉ
የአምላክ ልጆች ናቸው አንድም ሳይቀር ሁሉ
ደስታን አብሳሪ ምስራች ነጋሪ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ናልን ከሰማይ
በፊትህ መቆም
1. ያለህበት ቦታ ለካ ቅዱስ ነበር
ደፍሬ ቀረብኩት የማየውን ተአምር
በፊትህ የመቆም ሳይሆን ለአንተ ክብር
ምሥጢሩን ዘንግቼ ርቆኝ ሆኖ ስውር
ጫማዬን አወለቅሁ ማምለኬን ልጀምር /ዘፀ 3፡15/
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
2. ለመቆም በፊትህ ዕድሉ ተሰጥቶኝ
ግርማህን እንዳደንቅ ውበትህ መስጦኝ
ዘንግህን ዘርግተህ ሞገስህ እየጠራኝ
ምንኛ ክብር ነው አንተን እንዲህ መቅረብ
ስጦታህ ነው እንጂ ነጻ አድርገህ የምትስብ /አስቴር 5፡2/
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
3. በጌታ ፊት የሚቆም ማንነትን ይዘህ
መጠሪያህ አድርገህ ገብርኤል ነኝ ብለህ
ብስራትን ለመስጠት ቀና ልዑክ ሆነህ
በመንፈስ አንድ ሆነህ የላከህን መስለህ
የእርሱን ክብር ገለጽክ ደኀንነትን አውጀህ /ሉቃ 1/
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
4. የማልጠብቀውን ልዩ ትኩረት ሰጥተህ
በስሜ ጠራኸኝ ከዛፍ ውረድ ብለህ
ጸያፍ ሆኖ ሳይታይ ምኔም ሳይቀርህ
መቆሜ በፊትህ ሲያበቃኝ ለክብርህ
ልቤን ክፍት አደረከው ለጋስና ርኀሩኀ /ሉቃ 19/
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
5. በቤትህ ፊት መቆም ሁሌ የምመኘው
ልብን የሚማርክ ውስጥን ሚያረካው
ነጻ ወይ እስረኛ ለይቼ ሳላውቀው
ምክንያት የሚያነሳሳ ይኼ ነው የምለው
መለየት አስችለኝ መንፈስ የሞላውን
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
ምሥጋናችን ይመርልን
ምሥጋናችን ይመርልን ያርግልን /2/
ለእግዚአብሔር ቅዱስ ዙፋን
ይድረስልን /2/
ይድረስልን /2/ ያርግልን
ለአምላካችን ለጌታችን ለወደደን
ለእግዚአብሔር ዙፋን /2/
ለእግዚአብሔር ይሁን
ይኸው ይድረስልን
1. ከመላዕክቱ ጋራ ቅዱስ እንደሚሉት
ጠዋትና ማታ እንደማይሰለቹ
እኛም ፊቱ በምስጋና እንቀርባለን ኦሆ
እንቀርባለን አሀ
ለእግ/ር ይመርልን በዙፋኑ ያርግልን
ያርግልን አሀ
ይድረስልን /2/ ያርግልን
ለአምላካችን ለጌታችን ለወደደን
ለእግዚአብሔር ዙፋን /2/
ለእግዚአብሔር ይሁን
ይኸው ይድረስልን
2. በፀናች መንግስቱ ጥንትም ለነበረው
ከሰማያት በላይ ላለው ለሚኖረው
ይድረስልን ይመርልን ምስጋናችን ኦሆ
ምስጋናችን አሀ
ለእግ/ር ለጌታችን ላምላካችን ኦሆ
ላምላካችን አሀ
ይድረስልን /2/ ያርግልን
ለአምላካችን ለጌታችን ለወደደን
ለእግዚአብሔር ዙፋን /2/
ለእግዚአብሔር ይሁን
ይኸው ይድረስልን
3. ብድራቱ ይሁን ላደረገልን
ይህም ከመጠነው ማመስገናችን
ይንገስ ይንገስ ለዘላለም
እንደ እግ/ር ሐያል የለም
እንደ እግ/ር አሀ
በዙፋኑ ይኑርልን ምስጋናችን ይመርልን
ያፍስስልን አሀ
ይድረስልን /2/ ያርግልን
ለአምላካችን ለጌታችን ለወደደን
ለእግዚአብሔር ዙፋን /2/
ለእግዚአብሔር ይሁን
ይኸው ይድረስልን
