በሰማይና በምድር ከፍ ያልከው
ስልጣናት ክብር
ሁሉም የአንተ ነው /2x/ አሜን
- በሰማያት በዙፋንህ
እናክብርህ እንወድስህ
ሌላ ቋንቋ
ስለሌለን ጌታ ክበር እንላለን
2. ቃልኪዳኑን የሚያፀና
ከአንተ በላይ የለምና
ባለግርማ ባለሞገስ
እግዚአብሔር ሆይ ስምህ ይንገስ
3. በፍቅር ሐይል ማርከኸናል
ልትወደስ ይገባሐል
የዘላለም አምላካችን
መስዋት ይኸው ምስጋናችን
የዘላለም አምላካችን መስዋት ይኸው ጭብጨባችን
የዘላለም አምላካችን መስዋት ይኸው ሽብሸባችን
የዘላለም አምላካችን መስዋት ይኸው እልልታችን
