አይሆንልኝም ከቶ አይሆንልኝም
አንተን ሳልጠራ መሽቶ አይነጋልኝም
አይሆንልኝም እኔ አይሆንልኝም
አንተን ሳልጠራ ነግቶ አይመሽልኝም
1.ጠዋት ተነስቼ ነቅቼ
ሀይሌም ሳይበተን ተክቼ
አፌን እከፍታለሁ ስናገር
የኔ ጌታ አንተን በማክበር
ሲመሽም ይመጣል ይፈሳል
ያመልካም ስምህ በአንደበቴ
መች ይሆንልኛል ልረሳህ
ማን አለ ያላንተ አባቴ
2.ስጨነቅ ስጠበብ ስቆዝም
ስከፋ ተስፋዬ ሲጨልም
ትውስታዬ አንተ ነህ መድህኔ
ሌላ ረዳት የለኝ ከጎኔ
አንዳች ቀልድ አልሻም በአንተ
እኔ አይሆንልኝም ያለ አንተ
ስምህን ጠራለሁ ጠዋት ማታ
ከቶ አያምርብኝም ዝምታ
3.ዛሬ ስንቱ ከንቱ ያደርጋል
አምላኩን ጣኦቱን አስቀምጦ
ሙሉ ቀን ይውላል ያመሻል
ይህን የማይሰማ ይጠራል
እኔ ግን አልጠራም ያላንተ
ሲነጋና ስመሽ ጊዜያቱ
መች በዋዛ ልስት ልታለል
በርቶልኛልና እውነቱ
አይሆንልኝም ………
