የምሥጋና ቀን ነው ለእኛ ዛሬ

-

1. በወጀብ ባውሎ ንፋስ ውስጥ ስንጐሽም ስንገፋ
ደረሰልን የእኛ ጌታ ታዳጊው የእሥራኤል ተስፋን
ሞገዱንም ገሰጸልን ማዕበሉንም ጸጥ አረገው
እልል እንበል እናመስግን ዛሬ የደስታችን ቀን ነው

አዝ:- የምሥጋና ቀን ነው ለእኛ ዛሬ
የአዲስ ቅኔ የዝማሬ
ኑ እናመስግን ጌታ አምላካችንን
ሰርቶልናልና ስራችንን /2x/

2. ከአቅማችን በላይ ከብዶን የሚረዳን ወገን አጥተን
ረዴታችን መጣልን የያዕቆብ አምላክ አሰበን
በአዲስ ቅኔ በዝማሬ በከበሮ እናስተጋባ
ሥራችንን ሠርቶልናል ምሥጋናችንን እናግባ

አዝ:- የምሥጋና ቀን ነው ለእኛ ዛሬ
የአዲስ ቅኔ የዝማሬ
ኑ እናመስግን ጌታ አምላካችንን
ሰርቶልናልና ስራችንን /2x/

3. ቁጣው ነዶ በላያችን የተመኘው ለሞታችን
በቆፈረው ጉድጓድ ገባ አመጸኛው ጠላታችን
ስለዚህ እንውጣ ዛሬ በእልልታ እየዘመርን
እስትንፋስ ያላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እናመስግን

አዝ:- የምሥጋና ቀን ነው ለእኛ ዛሬ
የአዲስ ቅኔ የዝማሬ
ኑ እናመስግን ጌታ አምላካችንን
ሰርቶልናልና ስራችንን /2x/

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top