ቅዱስ ቁርባን የሕይወቴ ምግብ
የተራበችን ነፍስ የምታጠግብ /2/
እየሱስ ነህ አምንሀለሁ
እሰግድልሀለሁ እቀበልሃለሁ
ና ግባና በልቤ ኑር
የሕይወቴ ንጉስ ክበር ክበር
1. ወደ አንተ እራት የተጠሩ
ብፁአን ናቸው የተማሩ
የእግዚአብሔር በግ እየሱስ
በእውነት አንተ ነህ ቅዱስ
ቅዱስ ቁርባን የሕይወቴ ምግብ
የተራበችን ነፍስ የምታጠግብ /2/
እየሱስ ነህ አምንሀለሁ
እሰግድልሀለሁ እቀበልሃለሁ
ና ግባና በልቤ ኑር
የሕይወቴ ንጉስ ክበር ክበር
2. ወደረከሰችው ቤቴ
መግባት አይገባህም የሱሴ
ግን ስለጥበበኛው ስራህ
ቀርቤአለሁ ልቀበልህ
ቅዱስ ቁርባን የሕይወቴ ምግብ
የተራበችን ነፍስ የምታጠግብ /2/
እየሱስ ነህ አምንሀለሁ
እሰግድልሀለሁ እቀበልሃለሁ
ና ግባና በልቤ ኑር
የሕይወቴ ንጉስ ክበር ክበር
3. ያ የቆሸሸው ልቤ
ገብተህ ስታርፍበት በውስጤ
ይኸው ለመለመች ነፍሴ
አመስግናለሁ ንጉሴ
ቅዱስ ቁርባን የሕይወቴ ምግብ
የተራበችን ነፍስ የምታጠግብ /2/
እየሱስ ነህ አምንሀለሁ
እሰግድልሀለሁ እቀበልሃለሁ
ና ግባና በልቤ ኑር
የሕይወቴ ንጉስ ክበር ክበር
4. ምንም ደግ ሥራ ሣይኖረኝ
ግን በፍቅርህ ተዋሃድከኝ
ከሕዝቦችህም አንድ አደረከኝ
በክብር ልያዝህ እርዳኝ
ቅዱስ ቁርባን የሕይወቴ ምግብ
የተራበችን ነፍስ የምታጠግብ /2/
እየሱስ ነህ አምንሀለሁ
እሰግድልሀለሁ እቀበልሃለሁ
ና ግባና በልቤ ኑር
የሕይወቴ ንጉስ ክበር ክበር
