በእውነት ፍቅር አየን ድንቅ ፍቅር አየን
በቀራኒዎ ላይ የሱስ የፈፀመው
ለኔ ላንተ ላንቺ እስከሞት የወደደን
ለኔ ነው ላንተ ነው ላንቺም ነው
ኢየሱስ የሞተው
መርገሜን ከላዬ የሱስ አስወገደው
በእኔ ፋንታ ሞቶ ሐጥያቴን ሻረው
የፍቅሩ ምላሽ የለኝ የምከፍለው
ውስጤ የተሞላው ግርምት ዝምታ ነው
በምን ይገለፃል የፍቅሩ ብርታቱ
የሱስ የፈፀመው ሲታሰብ በውነቱ
ጠላቱን የሚወድ ያውም ነፍሱን ሰጥቶ
ቢፈለግ ቢታሰስ አይገኝም ከቶ
ለኔ ነው ለአንተ ነው
ላንቺም ነው ኢየሱስ የሞተው
አስቤ አጥንቼ አውርጄ የገባኝ
እንደየሱስ ፍቅር የለም የገጠመኝ
በዘመኔ ሁሉ የምመሰክረው
እውነተኛ አፍቃሪ ኢየሱስ ብቻ ነው
