ለመታሰቢያዬ አድርጉት

11

ሐሙስ ለት ማታ ጌታ የመሰረተው
ለመጨረሻ ግዜ እራሱን የሰጠው
ያደረገው እራሱን መስዋእት ለሰዎች
ሐጢያትንም ከጥፋቱ ለመመለስ እንዲመች

አለ ጌታችን በቃሉ እንካችሁ ስጋዬን
ለመታሰቢያዬ አድርጉት
ለዘለአለም ይህንን
እንዲሁም አባዝቶ ባረከው ደሙን
ለመዋጀት ዳግም ሐጥያተኞችን

ስጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ
ሐጥያትን ሸሽቶ ወደኔ የመጣ
ይኖራል ሁልግዜ ከእኔ ጋር በመንበር
ላይታክት ኢየሱስ ለህዝቡ ይል ነበር

ለህዝብ እስራኤል መናውን አውራጿል
እኛም በስጋው በደሙ ዋጅቶናል
ሁላችንም ለፅድቅ ለክብር ይጠራናል
ቅዱስ ቁርባን በእኛ እንዲከብር ይሻል

እኛንም ለመመለስ ከጥንት ኑሮአችን
እንቅረብ ወደጌታ በፍፁም ልባችን
ለማስደሰት በእውት ጌታ አምላካችንን
መቀበል አለብን ቅዱስ ሚስጥርህን

ህይወት ያለኢየሱስ እንደሌለ አውቀን
በሰራነው ሐጥያት ፍፁም ተጸጽተን
ማገልገልም ካሻን ኢየሱስ ጌታችንን
ቅድስ ቁርባን ኣለ ጋሻ መከታችን

መኖር ከፈለግን ዘለአለም ከእርሱ ጋር
ላለመኖር ካሰብን በምድር ተላላ
ማስደሰት ከፈለግን ወድሞቻችንን
ቅዱስ ቁርባን ለኛ ይሆናል ጋሻችን

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top