ፍቅር ይዞት ይህ ቸር የፍቅር ጌታ
በበረት ውስጥ ስለኔ ተንገላታ
በፍግ መሐል ስለኔ ማልዶ በሌት
ፍጥረት ሁሉ ለእርሱ ያደረገ ሐሴት
ስብራት የማያውቅ ይህ የህማም ሰው
ውስጣዊ ልቤን እንዴት ዳሰሰው
ተንቆ ቢኖር በሰው ተጠልቶ
አልተመለሰም ስራውን ከድቶ
እንደጠቦት በሸላቾች ፊት ዝም አለ
ሸክማችንን መድሐኒታችን ቻለ
አፋን ሳይከፍት በጠላቶቹ ሳይዘብት
ፍቅርን ለብሶ መስቀሉን አሸከሙት
ጐልጐታ ወጣ ሲድህ ሲቧጥጥ
ምድርም ሲፍቀው ገላውን ሲልጥ
የሐዘን ቀን ነው ሆኖም የደስታ
እርሱ ተረግሞ እኛን ሲፈታ
አለም በሌት በታላቅ መዳን ነቃ
ሐይል መጣና በአለም ንጉስ ሲቃ
ነፍሱን ሰጠ ይህ ቅዱስ የእግዚአብሔር በግ
ከሐጥያት እኔን ፈፅሞ ሊያድን
በቀትር ሲጮህ አባቱን አጥቶ
ፃድቃን አጣ ምድር ተከፈቶ
ስጋውን ከፍሎ ጥሎ ለሻረው
ለምን ይሸሻል ሰው ከፈጣሪው
