ደሙን እንደ ውሃ

12

ደሙን እንደ ውሃ ጐረፈ/2/
የጌታ ጀርባ በጅራፍ ተገረፈ
እግሩ እስኪነቃ ተራራውን ነጐደ
እስከሞት ድረስ ጌታ እኔን ወደደ

በዚያች ሌሊት ሲያለቅስ ሲያነባ አደረ
መድሐኒቴ በደም ላብ ተነከረ
ሁሉም እያለው ሆኖ እንደሌለው
የእኔ ፍቅር እጅግ ደሃ አደረገው

ክብር ሳያንሰው ሆኖ ለእኔ ችግረኛ
ፍቅር አሞኘው እኔን ወዶኛልና
ቃተተ ለእኔ በመስቀል ላይ እንዳለ
የእኔ ጌታ ከሞት ጋራ ታገለ

ፍፁም ታገሰ መከራውን በሙሉ
እኔን እንዲፈውስ በተወጋው ጐኑ
ተንገላታ ያለልክ ተጐሳቆለ
ያንን ሁሉ ፍቅር ነውና ቻለ

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top