ንሳሃቸው ላልወረደላቸው
ከባድ ሐዘን ለወደቀባቸው
መከራቸው ላላለቀባቸው
ያአንቺ ምህረት ተስፋ ይሁናቸው
ኦ ማርያም
ምንጩ አንቺ ነሽ ለፍፁም ንፅህና
ሁሉን ንፁህ ታደርጊያለሽና
ዘርጊላቸው እጅሽን በጤና
እለት እለት ይጨነቃሉና
ኦ ማርያም
መሸሻችን ወደአንቺ ዘንድ ነው
ያውቃሉና እንድታድኛቸው
ፊትሽን አይተው መኖር ፈልገው
ዘለአለም ደስ ደስ እንዲላቸው
ኦ ማርያም
በአንቺ እጅ ነው ሰማይ መከፈቱ
ያላንቺማ ይጠፋል ፍጥረቱ
አይፈታም ያላንቺ ሰሰለቱ
አንቺ አውጫቸው ከታሰሩበቱ
ኦ ማርያም
የፃድቃን ህግ ጎዳና መሪያቸው
ለታመኑሸ በእውነት ሕይወታቸው
ሙታንንም ዘወትር ጎብኛቸው
ከልጅሽ በጣም አማልጃቸው
ኦ ማርያም
እንባችን የሚወርደውን
ተመልክተሸ አንቺ እናታችን
ነበልባሉ ይጥፋ በይልን
መኖሪያችን ሰማይ እንዲሆን
ኦ ማርያም
በፍርድ ቀን በሌለበት መድሎ
ሲፈራረድ ሁሉም ተጠቅልሎ
ለኛ ድልን ለምኝልን ቶሎ
እንዲደርሰን እጣችን ተብሎ
ኦ ማርያም
