ጎልጎታ ወጣ የመርገም እንጨት ተሸክሞ
ደፋ ቀና እያለ በመገረፍ ብዛት ደክሞ
እኛንና እናንተን በፍቅሩ ሊዋጀን
በመስቀል ላይ ሆኖ ኢየሱስ ነው ያዳነን
እኛን ለማዳን ነው እንዲህ መዋረዱ
በበትር ሲመታ በየመንገዱ
ሐጥያት ሳይኖርበት ሐጥያተኛ ሆነ
ስለእኛ ብሎ እራሱን ኮነነ
እኛን ፀጋ ሊያለብስ ልብሱን ተገፈፈ
በግንድ ላይ ታስሮ እጅግ ተገረፈ
በጥፊ መቱት ምራቅም ተፋበት
ስቀለው እያሉ ያለምክንያት ጠሉት
የፈጣሪ እጆች በፍጡር ደቀቁ
ጌታቸው መሆኑን እነርሱ አላወቁ
ጨክነው ሰቀሉት በሚስማር ቸክረው
እርሱ ግን ፀለየ አባት ሆይ ማራቸው
እጅግ ተሰቃየ ለብዙ ሰአታት
ኮምጣጤ ቀመሰ ሲቃጠል በጥማት
ኤሎሄ ኤሎሄ እያለ ቃተተ
እንዲህ ተሰቃይቶ የማይሞት ሰው ሞተ
