መስቀል ተሸክሞ

16

መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሳ
ተደመሰሰለት የሰው ልጅ አበሳ

1. እርሱ ፍጹም ቅዱስ ፈጣሪ ነበረ
ከወንበዴ መሃል ሆኖ ተቆጠረ
በእንጨት የሚሰቀል የተረገመ ነው
ጌታዬ ስለ እኔ የከፈለው ይህ ነው

መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሳ
ተደመሰሰለት የሰው ልጅ አበሳ

2. በሰው ልጆች ኃጢያት በመተላለፍ
እንደ በደለኛ ሆኖ ሲገረፍ
ያን እለት በቁስሉ ቁስሌን ፈወሰልኝ
በሞቱ ሕይወቴን ከሞት አዳነልኝ

መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሳ
ተደመሰሰለት የሰው ልጅ አበሳ

3. እዳዬን ከፈለ ቀራኒዮ ውሎ
በሌቦች መካከል ጌታዬ ተሰቅሎ
የሱስ አልፎ ሲሰጥ ጠላቴም ወደቀ
እዳዬን ለመክፈል እሱ ግን ደቀቀ

መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሳ
ተደመሰሰለት የሰው ልጅ አበሳ

4. የጠፋን ነበርን እያንዳንዳችን
ሞቶ ባያድነን መድኃኒታችን
ሰውን ለመፈወስ በጅራፍ ተገርፎ
ለኛ ጤና ሰጠን እጅግ አትረፍርፎ

መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሳ
ተደመሰሰለት የሰው ልጅ አበሳ

5. ለሟች ሕይወት መስጠት የሚችለውን
ለበዳይ ይቅርታ የሚሰጠውን
እፎይ ትል ነበረ ብታገኝ እሱን
ዛሬም ይጠራሃል ስማው ጥሪውን

መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሳ
ተደመሰሰለት የሰው ልጅ አበሳ

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top