በመስቀል ተሰቅለሀ ነፃ ያወጣኸን
ቀንበራችን ሰብረህ ከሐጥያት ያዳንከን
በደከመን ጊዜ ማረፊያ የሆንከን
ክበር አምላካችን ክበር
ክበር ጌታችን ክበር
ከከበደን ሸክም አምላክ ሆይ የምታቃልልልን
ከመከራ ስቃይ ጌታ ሆይ የምትደግፈን
ስንተክዝ ስናዝን ጌታ ሆይ ምትረዳን ኣንተ ነህ
ምን እንከፍልሐለን አምላክ ሆይ ለሃያሉ ስምህ
አፅናኝ አባታችን ይመስገን ሁሌም ይመስገን
ደጋፊ አምላካችን ይመስገን ዛሬም ይመስገን
ተስፋ ቆርጠን ሳለ አምለክ ሆይ ዕረዳት የሆንከን
በሃጥያት ግዞት ውስጥ አንተ ነህ ዋስትና የሆንከን
ቀንበራችንን ሰብረህ አምላክ ሆይ ነፃ ያወጣኸን
የእስራኤል አምላክ ጌታችን ዛሬም ክበርልን
አፅናኝ አባታችን ይመስገን ሁሌም ይመስገን
ደጋፊ አምላካችን ይመስገን ዛሬም ይመስገን
ፀሎታችንን ሰምተህ አምላክ ሆይ መልስም ትሆናለህ
እኛንም ለማዳን ጌታ ሆይ ፈውስን ትሰጣለህ
ከቶ ምን አለና አባት ሆይ ለኛ ያላረከው
አንድ ልጅህንም ጌታ ሆይ በፍቅር የሰዋኸው
አፅናኝ ኣባታችን ይመስገን ሁሌም ይመስገን
ደጋፊ አምላካችን ይመስገን ዛሬም ይመስገን
