እናት ኢትዮጵያ እጇን ዘርግታለች
ቀድሞም ሆነ ዛሬ አቤቱ ትላለች
በመሬት ላይ ያለው በሙሉ ፍጥረት
በፍቅርህ ይኑር በሰላም ህብረት
በመሬት በአየር በባህር ለሚጓዘው
ሰላምና ደስታ ምረትን ስጠው
በሰዎች መካከል ትብብር እንዲነግስ
እባክህ ላክልን የሰላምን መንፈስ /2/
እንስሳት እፅዋት ፍጥረታት በሙሉ
ሁሉም ለአንተ ስም ይንበረከካሉ
እኛ ግን በትዕቢት ብንል አንገዛም
ጌታ ሆይ አትንፈገን ምሕረትና ሰላም /2/
በሰቃይ ላይ ላሉት በጦርነት ንዳድ
ተስፋ ለቆረጡት አተው የአንተን መንገድ
ጌታ ሆይ ስጠን አትበል ዝም
የአለምን ሳይሆን የአንተን ሰላም /2/
