ወደ ቤትህ ምራት

26

እንግዳ አይደለሁም ልምጣ ብዬ እልመጣ
የአንተ ቤት ክፍት ነው ለሚገባ
እንግዲህ ጌታ ሆይ ህይወቴን አስባት
ወዳንተ ጎዳና ወደቤትህ ምራት

ከባህር ይልቅ ሰፊ ነው ሰማያትን ያልፋል
ፍቅሩ ግን ጌታዬ እጅግ ጥልቅ ነው
ነፍሴን ኣስገዛለሁ ስለ ምህረቱ
ደስ ብሎኝ ኖራለው ዘወትር በቤቱ

ምራት ጌታ ሆይ ምራት
ምራት ኢየሱስ ሆይ ምራት
ወዳንተ ጎዳና ወደቤትህ ምራት

ከመኮብለልና ከጥፋት ድኛለሁ
እኔም ስለጌታ እመሰክራለሁ
የዘላለም ህይወት ከርሱ አግኝቻለሁ
ሁል ጊዜ የሱ ነኝ በእርሱ እኖራለሁ

ሁልጊዜ በጌታ እኔን ደስ ይለኛል
እንድጨነቅ እንኳን መች ተፈቅዶልኛል
ሁሉን ማከናወን የኔ ስራ አይደለም
ጌታ ነው ኤልሻዳይ የሚሳነው የለም

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top