አቅም የለኝም በራሴ
በአንተ ነው እዚህ መድረሴ
አሁንም ልቤ በአንተ ላይ
ጽኑ ነው ሁሌ በአንተ ይታመናል
እኔማ እራሴን አውቀዋለሁ
ያላንተ ከቶ እንደማልችለው
ያለፍኩት ያን ሁሉ በሕይወቴ
ኢየሱስ ሆነህ እረዳቴ
ምታመንበት የለም ዙሪያዬ
የምደገፈው ይህ ኣለኝ ብዬ
እኔ የለመድኩት የአንተን እጅ ነው
ዛሬም ተስፋዬ አንተን ጠብቃለሁ
አልችልም አልቆምም በራሴ አቅም የለኝም
አንተ ነህ ብርታቴ መመኪያ ሌላ የለኝም
የምደገፍብህ አስተማማኝ ለእኔ አለቴ
እመካብሃለሁ ሆነሀል ለእኔ ጉልበቴ
እኔ ያለአንተ አያስችለኝም
አንድ እርምጃ እንኳን አያስኬደኝም
በአንተ እጅህ ጌታ መውጣት መግባቴ
ዛሬን የቆምኩት ፀንቶ ጉልበቴ
ገብቶኛል ከእንግዲህ የኑሮዬ መሰረቱ
ከጭንቄ ማምለጫ መፍትሔ መላ ብልሐቱ
ሳልፈራ ሳልሰጋ በአንተ ላይ ተደላድዬ
ኑሮዬን እኖራለሁ ሐሳቤን በአንተ ላይ ጥዬ
