አቤቱ ደክሜ እንዳልወድቅ በፀጋህ ደግፈኝና
አድርሰኝ ወደፂዎን አገር የደምህ ካሳ ነኝና
ቢሆንም ዘመኑ ክፋ አውቃለሁ አንተ ካለኸኝ አሸናፊ
ዘወትር ድምፅህን ልስማ ጌታ ሆይ ዝም አትበለኝ
መስቀል ተሸክሜ ኋላ ልከተልህ ወስኛለሁ
ምንም ነገር ሳያጓጓኝ አንተን አስበልጬሃለው
ተሰናክዬ እንዳልወድቅ በፀጋህ ደግፈኝና
ወደ ተስፋ ሐገሬ አድርሰኝ ደስታዬ በዚያ ነውና
የማይጠፋ ደስታ ሰላም በሞላበት
ሃዘን ስቃይ ጭንቀት ማይታሰብበት
ካንተ ጋር መኖሩን በጣም ናፍቂያለሁ
ማራናታ ጌታ ቶሎ ና እላለሁ
ፍፃሜዬን አሳምረው አይኔ እንዳያይ ወደሌላ
አንቆ እንዳያስቀረው ዛሬ የአለም እሾ አሜኬላ
አሸናፊ ሕይወት ስጠኝ በቀረኝ ዘመኔ ጌታ
በምንም ሳልሰናከል ከዓላማዬ ሳልገታ
ማስተዋልን ስጠኝ ጥበብ ጨምርና
ማለፍን እንድችል ያዓለምን ፈተና
በትእግስት ልጠብቅ በመጠበቂያዬ
በራሴ ኣልችልም አግዘኝ ጌታዬ
አንተ ባለህበት በዚያ ለዘለአለም እኖራሁ
ፊት ለፊት አንተን እያየሁ ድካሜንም እረሳለሁ
ከእዕላፍ መላዕክት ጋራ ዙፋንህን እከብና
ከፍ ከፍ አደርግሃለው በአምልኮ በምስጋና
አምናለሁ አንድ ቀን ሆኜ ካንተ ጋራ
ምንም ሳልጨነቅ በምንም ሳልፈራ
የዛሬ ናፍቆቴን በእምነት አየዋለሁ
የዘላለም ሃሴት ያኔ አደርጋለሁ
