አብ እኔን እንደላከኝ
እኔም ደግሞ እናንተን
እልካችኋለሁ
አድርሱ መልክቴን
ወደ አለም ሁሉ ሂዱ
የወንጌሉን ፍም አንድዱ
እኔም ከአናንተ ጋር አለሁ በመንገዱ
አትጠራጠሩ አምላክ ነኝ ተረዱ
ለታወሩት ብርሃንን
ለድሆች መልካም ዜናን
በመንፈስ በእውነት
ደስታውን አብስሩ
ይፈቱ ይዝለሉ በሱስ የታሰሩ
የሚጓዙ እኔን አምነው
መርዝም እንኳን አይጐዳቸው
በስሜ አጋንንት ችለው ያወጣሉ
በሽተኞች ሁሉ ፍፁም ይድናሉ
በአብ በወልድ በመንፈስም
አጥምቋቸው በሉ ሁሉንም
ትዛዛቴን ሁሉ በመፈፀም ይትጉ
እኔም ከእናንተ ጋር መሆኔን አትዘንጉ
