አፅናኛችን መንፈስ ቅዱስ
የእውነት መንፈስ
ዛሬም ነገም ለዘለአለም ቅዱስ /3/
ከፍቅር በላይ ነው ለኛ ያለህ ጌታ
መንፈስ ቅዱስህን ልከህ እንዳንገላታ
አረስርስህ ያዘው ነፍሳችንን
ማንም ያላየውን እኛ ግን አየን /4 /
ወዳጅ እንደሌለው አትሆንም ያለው
ለካ ሊያበረታን ሊያደርገን ነው ህያው
ሁሌም በልቡ ውስጥ እኛን ተሸክሞ
በፍቅር አዋድደን በመንፈሱ አትሞ /4/
ይህን ሁሉ ላደረገው ቸር አባት
ይኽው ዝማሪያችን ይሁን መስዋት
አሁንም አብዛልን ጌታ ጨምርልን
አፍስስልን መንፈስህን ያ መፅናኛችንን /4/
አልፋና ኦሜጋ ፍፃሜ የሌለህ
የዘለአለም አምላክ እየሱስ አንተ ነህ
አባት ሆይ ልጆችህ ምስክሮችህ ነን
አንተው በላክልን መንፈስህ ተሞልተን /4/
