ስምህ ይክበር

64

ስምህ ይክበር ይመስገን ይጠራ
በእረፍት ቦታዎች እንዲሁም በስራ
በምድር በሰማይ ያሉ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሐያል ነው ይበሉ

በቤት ውስጥ ያለ በሜዳ የሚሰራ
የአንተን ክበርና ታላቅነት ያውራ
ቀና ብሎ ያመስግን ያለው በጦርነት
ከአንተ ያገኝ ዘንድ ሰላምና ምህረት

እንስሳት በሙሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ
ይድከሙ በያሉበት ስምህ እንዲታወቅ
እፅዋት በሙሉ በባህርና በምድር
ቀና ቀና ይበሉ ስለጌታቸው ክብር

በመቅደስህ በማለዳ ይነሱ
ከበሮ ጽናጽል መቋሚያውን ያንሱ
መለአክቶች ሁሉ ይቀኙ ለአንተ ስም
በሰማይ ምስጋና በምድርም ሰላም

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top