- ሁሉ ሞልቶ እያለው ስለኛ ክብሩን የተወው
ከሰማይ የወረደው በረት የተወለደው
እጅግ ተሰቃይቶ በጦርም ተወግቶ
በመስቀል የሞተው ኢየሱስ ጌታ ነው
ኢየሱስ ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው ጌታ ነው /4/
2. አውሩን ያበራው ሽባውን የተረተረው
አንካሳን ያዘለለው ለምጻሙን ያነጻው
ረሀብተኛን ያጠገበው የተጠማን ያረካው
ሙታንን ያስነሳው ኢየሱስጌታ ነው
ኢየሱስ ጌታ ነው
3. ሲኦል የወረደው አስረኛን የፈታው
ሰይጣንን የረታው ትጥቁንም ያስፈታው
ምርኮን የማረከው ሞትን ያሸነፈው
ኤልሻዳይ የሆነው ኢየሱስጌታ ነው
ኢየሱስ ጌታ ነው
4. ተጨንቀን እያለን ሰላም ለእናንተ ያለን
በብዙ ያጽናናን የተስፋ ቃል የሰጠን
በክብር ያረገው መንፈሱን የላከው
ዳግሞ የሚመጣው ኢየሱስ ጌታ ነው
ኢየሱስ ጌታ ነው
