አንተ አለህ ብሎ ለተማመነህ
አታሳፍርም አለሁ ትላለህ
የሚስኪን ወዳጅ ታማኝ ጓደኛ
የማትሸነግል ሁሌ እውነተኛ
አንተ ያደረገ የህይወት ጓደኛ
ዕጣው ያማረለት እሱ እድለኛ
መሰረቱ ሀረግ በእምነቱ የፀና
በድል ይራመዳል በሕይወት ጐዳና
አልተሳሳትኩም አንተን ማለቴ
የልቤ ርጫ ኢየሱስ እረዳቴ
ኮራሁኝ እንጂ መች አፈርኩብህ
በእኔ ላይ ሲሆን በጐ ሐሳብህ
ልቤን በፍረሃት ቢያሸብረው
ጠላቴ ቢዝት ውስጤን ቢያርደው
አልደፈርም አንተ አለህልኝ
ያስጨነቀኝ ምትረታልኝ
ይመሰክራል ዛሬ አኗኗሬ
እንደረዳኸኝ ኢየሱስ መድህኔ
አለኝ ምልክት የአንተ እርዳታ
ስኬቴ ሁሉ በአንተ ነው ጌታ
