እንደ ሙሴ ከውሃ ተገኘሁ
እንደ ዮሴፍ ለግብፃዊያን ተሸጥኩ
እንደ ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ተጣልኩ
አትንገሩኝ ተውት ከየት እንደሆንኩ
እኔም አላውቅም የእኔን እጣ
ተፅፌ እንዳለሁ ከማን ተርታ
ከፊት የሚቆምልኝ አለሁ ባዬ
ጌታ ነው ተያዥ ጠበኝዬ
አስቀድመህ ስትወስነኝ ስትመርጠኝ ለራስህ ክብር
አስደናቂ አደረከው የህይወቴን መልካም ጅምር
ክብር ይሁን ይሁን ላሰብክልኝ
ለኔ መልካም በጐ ላረክልኝ
ሞት ተፈርዶብኝ ተጥዬ በምድረ በዳ
አንተ ግን ተመለከትከኝ እንዳልሞት እንዳልጐዳ
አለበስከኝ የንጉስ ካባ ክብር
አነገስከኝ በባእድ አገር ክብር
