ከገመትኩት በላይ ሆነብኝ ውለታህ/2/
ካሰብኩትም በላይ ሆነብኝ ስጦታህ /2/
ስጦታዬ ከላይ ከበላዬ የተቸረኝ
ባስበው ከስሌት ከቁጥር ላቀብኝ
አልገባኝ እንጂ ባልረዳው
እርሱ ያውቀኝ ነበር እኔ ሳላውቀው
በእናቴ ማህፀን ያኔ የመረጠኝ
ታማኝ ኣድርጐ ለክብሩ ለየኝ
አማረልኝ እኔስ እጣዬ
መመረጤ በጌታዬ
ይስመርልኝ ፍፃሜዬ
ታማኝ ሆኜ ለጌታዬ
ሃይሉ በድካሜ ክብሩ ሲገልፀው
እኔን መረጠኝ ሃጥያተኛን ሰው
ፀጋው በዝቶልኝ ፊቱ ቆሚያለሁ
ያከበረኝን አክብረዋለሁ
ከርሱ ለርሱ ይኸው ቅኔ
ልቀኝለት ለመድህኔ
የማይገባኝን ብዙ በረከት
አጐናፀፈኝ በእርሱ ቸርነት
ህይወቴ ሆኗል የታምራት
የሚያየኝ ሁሉ የሚደነቅበት
ለዚህ ምላሽ ምን እላለሁ
ያለኝ ይኸው ተመስገን ነው
ለዚህ ምላሽ ምን እላለሁ
ያለኝ ይኸው ምስጋና ነው
