ያ ሁሉ አለፈ የተጨነቅኩበት
አንተ በእኔ ውስጥ የተናገርክበት
ለብዙ አመታት ሚስጥር የሆንክበት
ዛሬ ተገለጠ አንተ ልትከብርበት
ከፍ በል የኔ ጌታ
ከፍ በል ከፍ በል
አቀርባለሁኝ ምስጋና
ከዚህ በላይ ምን ልበል
እንባዬን ከዓይኔ ላይ አብሰኸኛል /2/
አንደበቴን ከፍተህ አዘምረኸኛል /2/
በከፍታዎች ላይ እግሬን አቁመሐል /2/
ተመስገን መድህኔ ክብር ይገባሃል
አንገቴን ቀና አድርገህ ጭንቀቴን ሰምተሃል /2/
እረፍት የነሳኝን ሸክሜን አቃለሃል /2/
ለጥያቄዎቼም መልስ ሆነህልኛል
ከፍ ከፍ ላድርግህ ፍቅርህ በዝቶልኛል /2/
ያልሆንከው ምን አለ ለኔ ያልሰጠኸኝ /2/
ህይወትህን ሳይቀር ቤዛ አደረክልኝ /2/
ከቃላትም በላይ እጅግም ወደድከኝ
በልብህ ዙፋን ላይ መርጠህ አስቀመጥከኝ /2/
